ዓለምአቀፋዊ ዜና

ዓለም ላይ ኮሮና ቫይረስ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር ከ22 ሚሊየን አለፈ

By Meseret Awoke

August 19, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም ላይ ኮሮና ቫይረስ ያለባቸው ሰወች ቁጥር 22 ሚሊየን ማለፉ ተነግሯል፡፡

ከዚህ ውስጥ አሜሪካ 5 ሚሊየን 481 ሺህ 557 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው ዓለም ላይ ቀዳሚ ሆናለች፡፡

እንዲሁም በብራዚል 3 ሚሊየን 407 ሺህ 354፣ ህንድ 2 ሚሊየን 702 ሺህ 742፣ ሩሲያ 930 ሺህ 276 እና ደቡብ አፍሪካ 592 ሺህ 144 ሰወች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰወች ቁጥርም ከ779 ሺህ በላይ ሆኗል ነው የተባለው፡፡

ወደ 14 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸውን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ