አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና የፓርቲው ፕሬዚዳንትና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሰጡት የሥራ መመሪያ ተጠናቅቋል።
የፓርቲው ም/ፕሬዚዳንትና የዋናው ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ እንዳሉት ÷ “በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሃሳብ ለብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቅቋል፡፡
ከጥቅምት 19 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአዳማና አዲስ አበባ ከተሞች የተሰጠው ስልጠና የፓርቲው ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሰጡት የሥራ መመሪያ በስኬት ፍጻሜውን አግኝቷል ብለዋል።
በመርሐ ግብሩ ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መሳተፋቸውን አቶ አደም ፋራህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
የአስተሳሰብ አንድነት ከመፍጠርና የተግባር አፈፃፀምን ከማላቅ አኳያ እጅግ ከፍተኛ ፋይዳ የተገኘበት ስልጠናው ÷ ፓርቲው እውነተኛ የሕብረ ብሔራዊነት ተምሳሌት መሆኑ በተጨባጭ የተንፀባረቀበት እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡
የስልጠና መርሐ ግብሩ ከዝግጅት እስከ ገለጻ፣ የቡድን ውይይት፣ የተሞክሮ ልውውጥ፣ የልማት ሥራዎች የመስክ ጉብኝት እና ማጠቃለያ ድረስ ዓላማውን በሚገባ አሳክቶ እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በዚህ መሰረትም አስተባባሪዎች፣ አሰልጣኞች፣ አወያዮች፣ የፀጥታ ተቋማት፣ የኦሮሚያ ክልል መንግስትና ልዩ ልዩ ተቋማቱ፣ የአዳማ ከተማ አስተዳደር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የስልጠናው ተሳታፊ አመራሮች በሙሉ ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!