አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ11ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ ቴክ ኮሚኒቲ ስቴዲየም በማቅናት ብሬንትፎርድን የገጠመው ኒውካስል ዩናይትድ 3 ለ 1 ሲሸነፍ አስቶንቪላ በአንጻሩ ቦርንማውዝን 4 ለ 0 አሸንፏል፡፡
11 ሰዓት ላይ በተከናወነው ጨዋታ የብሬንትፎርድን የማሸነፊያ ግቦች ሻዴ እና ኢጎር ቲያጎ (2) ሲያስቆጥሩ የኒውካስልን ብቸኛ ግብ ባርንስ ከመረብ አሳርፏል፡፡
በሌላ በኩል የአስቶንቪላን የማሸነፊያ ግቦች ቦንዲያ፣ ኦናና፣ ባርክሌ እና ዳኒኤል ማለን አስቆጥረዋል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ኖቲንግሃም ፎረስት ሊድስ ዩናይትድን 3 ለ 1 ሲያሸንፍ ÷ ክሪስታል ፓላስ እና ብራይተን ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡