አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልዕክት ÷ አንጋፋው የታሪክ ምሁር ላዺሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ማለፋቸውን በታላቅ ኀዘን ሰማሁ ብለዋል።
ነፍሳቸውን በዐጸደ ገነት እንዲያኖርና እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን እንዲሰጥ ተመኝተዋል፡፡