አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዜጎችን ከድህነት ወለል ለማውጣት በተከናወኑ ሥራዎች በርካታ ዜጎች ከተረጂነት ወደ አምራችነት ተሸጋግረዋል አሉ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ፈንታ ደጀን።
የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት እና ሥራ ፕሮጀክት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በቢሾፍቱ እየተካሄደ ነው።
ሚኒስትር ዴዔታው በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ መንግስት በ2017 በጀት ዓመት ለገጠር ሴፍቲኔት 45 ቢሊየን ብር እንዲሁም ለከተማ ሴፍቲኔት ደግሞ 15 ቢሊየን ብር ወጭ አድርጓል።
ዜጎችን ከድህነት ወለል ለማውጣት በተከናወነው ሥራ በርካታ ዜጎች ከተረጂነት ወደ አምራችነት መሸጋገራቸውን አብራርተዋል፡፡
የሴፍቲኔት ፕሮግራም ውጤታማ መሆኑን ተከትሎ 3ኛው ዙር እንዲቀጥል ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች 250 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል።
በመሳፍንት እያዩ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!