የሀገር ውስጥ ዜና

የጎርፍ አደጋን በጥናት ላይ ተመስርቶ በማስተዳደር ወደ ዕድል መቀየር ይቻላል – ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)

By Adimasu Aragawu

November 10, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጎርፍ አደጋን በጥናት ላይ ተመስርቶ በአግባቡ በማስተዳደር ወደ ዕድልና ውጤት መቀየር ይቻላል አሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)።

በሚኒስቴሩ ዘላቂና ውጤታማ የጎርፍ መከላከል ስራ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የመነሻ ጥናት ውጤት ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።

ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ የጎርፍ አደጋን በጥናት ላይ ተመስርቶ በአግባቡ በማስተዳደር ወደ ዕድልና ውጤት መቀየር እንደሚቻል ተናግረዋል።

ባለፉት ዓመታት በሚኒስቴሩ በሁሉም ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ተፋሰሶች አካባቢ ሰፊ ስራ ተሰርቶ ውጤታማ መሆኑን ገልጸው÷ በቀጣይ የጥናት ግኝቱን መነሻ በማድረግ ችግርንና አደጋን ወደ ዕድልና መልካም አጋጣሚ መቀየር እንደሚቻል ጠቁመዋል።

የጎርፍ አደጋ በአግባቡ መከላከልና ማስተዳደር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና የስነልቦና ችግሮችን የመፍታት አቅም እንዳለውም አመላክተዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ግኝቱ ላይ ጠቃሚ አስተያየት እንዲያቀርቡ እና የጥናት ግኝቱን ያቀረበው ኒኮላስ ኦ-ዲዋየር አማካሪ ድርጅት የሚነሱ አስተያየቶችን በቅንነት ተቀብሎ የጥናቱ አካል እንዲያደርግ አስገንዝበዋል።

በመድረኩ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ጌትነት ስሜ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!