የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ቱሪዝም ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው

By Yonas Getnet

November 10, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የቱሪዝም ድርጅት 26ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

በጉባዔው በቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክና በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) ተሳትፈዋል፡፡

ከጥቅምት 28 እስከ ሕዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም በሪያድ እየተካሄደ በሚገኘው ጉባዔ ከ160 አባል ሀገራት የተወጣጡ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ሌሎች እንግዶች ታድመዋል።

መድረኩ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘላቂና ሁሉን አቀፍ እድገትን ማፋጠን በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ለመምከር ያለመ ነው፡፡

በተጨማሪም በቱሪዝም ዘርፍ ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር እንደሚያስችል ነው የተገለጸው፡፡

ጉባዔው በኢትዮጵያ በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራበት የሚገኘውን የቱሪዝም ዘርፍ ይበልጥ ለማሳደግ ልምድ የሚቀሰምበት እንደሚሆን ተመላክቷል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!