ቴክ

የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላትን የያዘ መጽሐፍ ተመረቀ

By sosina alemayehu

November 10, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላትን በአማርኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች የያዘ መጽሐፍ በዛሬው ዕለት ተመርቋል። ‎ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዚዳንት በላይ ካሳ (ፕ/ር)፣ ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ‎ ‎በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ መጽሐፉ በየጊዜው እያደገና እየተሻሻለ የሚሄድ ዘመን ተሻጋሪ ሥራ ነው ። ‎ ሳይንሳዊ እውቀትን በሀገር ውስጥ ቋንቋ በመተርጎም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም አንስተዋል። ‎ ‎በመጀመሪያው ዕትም ከ11 ሺህ በላይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቃላት አቻ ስያሜ ለመስጠት ጥረት መደረጉ ተመላክቷል።

በሐይማኖት ወንድራድ