አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ቀብር ሥነ ሥርዓት በነገው ዕለት ይፈጸማል፡፡
የላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) አስከሬን ሽኝት መርሐ ግብር ነገ 5 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ እንደሚካሄድ ተመላክቷል፡፡
ሥርዓተ ቀብራቸውም ነገ 7 ሰዓት ላይ በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር እንደሚፈጸም አስተባባሪ ኮሚቴው ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
የታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ባደረባቸው ሕመም ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በትናንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወቃል፡፡
ላጲሶ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ የታሪክ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የተለያዩ የታሪክ መጽሐፍትን ለአንባቢያን አበርክተዋል፡፡
የኢትዮጵያውያንን የጋራ እሴት፣ ባሕልና ቋንቋ በማውሳት የሕዝቦች ታሪክ ጎልቶ እንዲታወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውም ተጠቁሟል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!