አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ባህል ስፖርት አባል ሀገር ከመሆን አልፋ የምክትል ፕሬዚዳንትነት ቦታን ማግኘቷ የሚበረታታ ነው አሉ የኢትዮጵያ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ።
የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴርን የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል፡፡
ሸዊት ሻንካ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ሚኒስቴሩ በስፖርት ልማት ዘርፍ ንቁ፣ ብቁ፣ ተወዳዳሪ እንዲሁም አሸናፊ ትውልድን ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው።
በየደረጃው ከት/ቤቶች እስከ ዓለም አቀፍ መድረክ ብዙ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው ÷ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ተሳትፎዎችን በማድረግ ዋንጫዎችን ማግኘት መቻሉን አመልክተዋል፡፡
ስፖርት የረጅም ጊዜ ሒደት ውጤት በመሆኑ ቀጣይነት ያለው ለውጥ ለማምጣት በታዳጊዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በቻይና ባደረገችው የባህል ስፖርት ፌስቲቫል በየዘርፉ ከፍ ብላ እያንሰራራች መሆኑ የታየችበት መድረክ እንደነበር ማብራራታቸውን ሚኒስቴሩ ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ባህል ስፖርት አባል ሀገር ከመሆን አልፋ የምክትል ፕሬዚዳንትነት ቦታን ማግኘቷ የሚበረታታ እንደሆነም አውስተዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!