የሀገር ውስጥ ዜና

የላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) የአስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው

By Adimasu Aragawu

November 11, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) አስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ እየተካሄደ ነው፡፡

በሽኝት ሥነ ሥርዓቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች የሥራ ባልደረቦችና ወዳጅ ዘመዶች ተገኝተዋል።

የላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ሥርዓተ ቀብርም ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ይፈጸማል፡፡

የታሪክ ተመራማሪው ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ (ፕ/ር) ባደረባቸው ሕመም ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወቃል፡፡

ላጲሶ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ የታሪክ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የተለያዩ የታሪክ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አበርክተዋል፡፡

የኢትዮጵያውያንን የጋራ እሴት፣ ባሕልና ቋንቋ በማውሳት የሕዝቦች ታሪክ ጎልቶ እንዲታወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውም ተጠቁሟል፡፡