የሀገር ውስጥ ዜና

32 የኦነግ ሸኔ አባላት ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው እጃቸውን ለመንግስት ሰጡ

By Tibebu Kebede

August 19, 2020

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 13 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 32 የኦነግ ሸኔ አባላት ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ እጃቸውን ለመንግስት ሰጡ፡፡

አባላቱ ኦሮሞን ነጻ እናውጣ በሚል ሽፋን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን የመግደል፣ የህዳሴውን ግድብ የማደናቀፍና ሌሎች የመሰረተ ልማት ተቋማትን የማጥቃት ተልዕኮ ተቀብለው እንደነበር ገልጸዋል፡፡