የሀገር ውስጥ ዜና

5ኛው ሀገር አቀፍ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ እየተካሄደ ነው

By Yonas Getnet

November 12, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 5ኛው ሀገር አቀፍ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በአርባ ምንጭ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ጉባዔው “ኃይማኖቶች ለሰላም፣ ለአንድነት እና ለአብሮነት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

ለሁለት ቀናት የሚቆየውን ጉባዔ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ፎረም እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኃይማኖት ተቋማት በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡

በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለን ጨምሮ የፎረሙ አባላት፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኃይማኖት ተቋማት አባላትና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

በዮሴፍ ጩሩቆ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!