የሀገር ውስጥ ዜና

20ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ወቅት የሚከበር ነው

By sosina alemayehu

November 12, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በርካታ ሀገራዊ አጀንዳዎች በጋራ በሚከናወኑበት ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ወቅት የሚከበር ነው አለ የፌዴሬሽን ምክር ቤት።

በም/ቤቱ የመንግሥታት ግንኙነት፣ የዴሞክራሲ አንድነትና የሕገ መንግሥት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ ፀሐፊ ባንቺይርጋ መለሰ እንዳሉት ፥ የቀኑ መከበር በሕዝቦች መካከል ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር ያስችላል፡፡

በተጨማሪም ዴሞክራሲያዊ አንድነት እንዲከበርና ሕብረ ብሔራዊነት እንዲጎለብት እንዲሁም ፌዴራላዊ አስተሳሰብና እሴቶች እንዲጎለብቱ ጉልህ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡

20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በርካታ ሀገራዊ አጀንዳዎች በጋራ በሚከናወኑበት ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ወቅት የሚከበር መሆኑን አውስተዋል፡፡

በዓሉ ከሕዳር 25 ቀን 2018 ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚከበር ሲሆን ÷ ሕዳር 29 ቀን ደግሞ የማጠቃለያው መርሐ ግብሩ በሆሳዕና ከተማ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በሰለሞን በየነ