ዓለምአቀፋዊ ዜና

10ኛው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት ዓመታዊ ጉባዔ በኢትዮጵያ ይካሄዳል

By Melaku Gedif

November 13, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ዓመታዊ ጉባዔ በፈረንጆቹ 2026 በኢትዮጵያ ይካሄዳል፡፡

9ኛው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት ዓመታዊ ጉባዔ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በተገኙበት በኒውዮርክ ተካሂዷል፡፡

በዚህ ወቅትም የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ለዓለም አቀፍ ሰላም፣ ደህንነት እና ዘላቂ ልማት አጋርነታቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ሁለቱ ወገኖች በመካሄድ ላይ የሚገኙ የትጥቅ ግጭቶች፣ ሰብዓዊ ቀውሶች እና የዓለም አቀፍ ሕግ መሸርሸር ላይ ጥልቅ ስጋት እንዳላቸው ገልጸው÷ልዩነቶችን ለመፍታት ውይይት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ተቋማቱ በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን፣ በሶማሊያ፣ በሊቢያ፣ በሳህል ቀጣና እና ሌሎች አካባቢዎች ያሉ አፍሪካ መር የሰላም ሒደቶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ሥራዎች፣ በአካታች ልማት እና በ2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባዔ ውጤቶች ላይ በትብብር መስራት እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡

ሰላም፣ ደህንነትና ዘላቂ እድገትን በማጠናከር የአፍሪካ ህብረት በሴቶች የሚደርሱ ጥቃቶችን ለማስቆም በትኩረት መስራት እንዳለበት አመልክተዋል፡፡

10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ዓመታዊ ጉባዔ በፈረንጆቹ 2026 በኢትዮጵያ እንዲካሄድ ስምምነት ላይ መደረሱንም የህብረቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!