የሀገር ውስጥ ዜና

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል የኢትዮጵያን ከፍታ በሚመጥን መልኩ ይከበራል – እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

By sosina alemayehu

November 13, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) 20ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል የኢትዮጵያን ከፍታ በሚመጥን መልኩ ይከበራል አሉ።

ርዕሰ መስተዳድሩ የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ በዓሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስተናጋጅነት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት እንደሚከበር ገልጸዋል።

በዓሉን ‘ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረብሔራዊ አንድነት’ በሚል መሪ ሃሳብ በሆሳዕና ከተማ ሕዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።

በዓሉ በኢትዮጵያ ከፍታ ልክ እንዲከበር የሚያስችል ሰፊ ዝግጅት መደረጉን አብራርተዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በተጠናቀቀበት እንዲሁም ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ኢትዮጵያ በጀመረችበት ዓመት የሚከበረው በዓሉ የሀገሪቱን የከፍታ ጉዞ የሚመጥን ሆኖ እንዲከበር ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት።

በሰለሞን በየነ