የሀገር ውስጥ ዜና

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል የሚጠይቀውን የዝግጅት ስራ ተመልክተናል – አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

By Yonas Getnet

November 14, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል የሚጠይቀውን የአመራርነት ጥበብ የሚያረጋግጡ የዝግጅት ስራዎችን ተመልክተናል አሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የፌዴራል የበዓሉ አቢይ ኮሚቴ 20ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል ዝግጅት እየገመገመ ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የበዓሉ ሁነቶች የሚከናወንባቸው ስፍራዎች፣ የእንግዶች ማረፊያ ቦታዎች፣ የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ የከተሞች የመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ያከናወናቸውን የዝግጅት ስራዎች ዙሪያ ገለጻ አድርጓል።

በዚህ መሰረት በሆሳዕና ከተማ ወደ 30 ሆቴሎች ተለይተው ደረጃቸው አሟልተው መዘጋጀታቸው ተብራርቷል።

በሆሳዕና ከተማ ሲፖዚየም የሚካሄድበት አዳራሽ፣ በወልቂጤ ከተማ የንግድ ኤግዚብሽን እና ባዛር ስፍራ ግንባታ ተጠናቅቋል።

ከ30 ሺህ በላይ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ስታዲየም ግንባታ መጠናቀቁን ያነሳው ኮሚቴው፤ የሆሳዕና ከተማን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሳደግ ተጨማሪ የጉድጓድ ቁፋሮና መስመር ዝርጋታ እየተደረገ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በጋራ ማዕድ የሚቆርሱበት የእራት ግብዣ ስፍራም መዘጋጀቱን ያመለከተው ኮሚቴው፤ ቀሪ ስራዎች የተሻለ የአፈፃፀም ደረጃ እንደሚገኙ አመልክቷል።

አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ያየናቸው የልማት ስራዎች የበዓሉ ትሩፋቶችን ያመላከቱ ናቸው ብለዋል።

የሚቀሩ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁና በዓሉን በተሳካ ሁኔታ ለማክበር የሚያስችሉ ሁኔታዎች በጥንቃቄ እንዲገባደዱ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በበኩላቸው በ15 ቀናት ውስጥ ቀሪ የዝግጅት ስራዎችና የልማት ስራዎችን እንደሚጠናቀቁ አረጋግጠዋል።

በዓሉ ከተስፋ ብርሃን ተሸጋግረን ወደ ሚጨበጥ ተስፋ ላይ መድረሳችንን የምንመሰክርበት ይሆናል ብለዋል።

በማርታ ጌታቸው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!