ስፓርት

ኪሊያን ምባፔ ወደ ማድሪድ ተመለሰ

By Adimasu Aragawu

November 14, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ26 ዓመቱ ተጫዋች ኪሊያን ምባፔ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ወደ ሪያል ማድሪድ ተመልሷል፡፡

ትናንት ምሽት ፈረንሳይ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዩክሬንን 4 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ ሁለት ግቦችን ቢያስቆጥርም ጉዳት አጋጥሞታል፡፡

በዚህም ተጫዋቹ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ስብስብን በመልቀቅ ወደ ክለቡ ሪያል ማድሪድ ለመመለስ ተገድዷል፡፡

ኪሊያን ምባፔ በቀኝ ቁርጭምጭሚቱ ላይ እብጠት እንዳጋጠመው የተገለፀ ሲሆን÷ ተጨማሪ የሕክምና ምርመራ በማድሪድ እንደሚደረግለት ነው የተጠቆመው፡፡

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጫዋች ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታ ሀገሩ ፈረንሳይ ከአዘርባጃን የምታደርገው ጨዋታ የሚያልፈው ይሆናል፡፡

ፈረንሳይ ትናንት ምሽት ዩክሬንን በማሸነፍ ለ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ውድድር ማለፏ ይታወቃል፡፡

በጨዋታው ሁለት ግብ ያስቆጠረው ኪሊያን ምባፔ በእግር ኳስ ሕይወቱ ያስቆጠራቸውን የግብ ብዛት ወደ 400 ከፍ ማድረግ ችሏል፡፡

በወንድማገኝ ፀጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!