አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ስፖርት በበርካታ ኃላፊነቶች ላይ አገልግለዋል፤ አሁንም እያገለገሉ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት፣ የአፍሪካ ፓርላማ አፈ ጉባኤ፣ የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት እና ሌሎችም የሰሩባቸውና እየሰሩባቸው ያሉ ኃላፊነቶች ናቸው።
በሙያ የጥርስ ሐኪምም የሆኑት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፤ በኢትዮጵያ የስፖርት ዘርፍ ውስጥ ከ20 ዓመታት በላይ የዘለቀ ታሪክና የአመራርነት ተሳትፎ አላቸው።
ከፋና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ አትሌቲክሱን በተመለከተ ሲገልጹ የኢትዮጵያ አዳጊ ወጣቶች ጨዋታ በርካታ ተተኪዎች የሚገኝበት መድረክ ነው ይላሉ።
በኦሎምፒክ ውድድሮች ወቅት የሚነሱ ጉዳዮች በአትሌቶች ሥነ ልቦና እና ተተኪ በመፍጠር ሂደት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥር በመሆኑ በትኩረት ማየት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ብሔራዊ ቡድን፣ ብሔራዊ አትሌት፣ ብሔራዊ አሠልጣኝ፣ ብሔራዊ የስፖርት ሆቴል ፈርሷል ያሉት ዶ/ር አሸብር፤ ይህንን መልሶ ለመጠገን ቁርጠኝነት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
አሸናፊ የሆነ ብሔራዊ ቡድን መፍጠር አለብን በማለት አሁን ላይ በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑንም አመልክተዋል።
በበቀጣዩ ኦሊምፒክ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ከባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በትብብር እየሰራን ነው ብለዋል።
በቅድስት ዘውዱ
ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ከፋና ፖድካስት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ 👉 https://www.youtube.com/watch?v=3wxgkEkC3yU