አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ማስፋፊያ ግንባታ የታካሚዎችን አገልግሎት በእጥፍ ያሳድጋል አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡
ከንቲባ አዳነች በአንጋፋው ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል አዲስ ሆስፒታልን የሚመጣጠን ማስፋፊያ በመገንባት ዘመናዊ የሕክምና መሳሪያ አሟልተን ሥራ አስጀምረናል ብለዋል።
በሆስፒታሉ የተገነባው የላቀ የሕክምና ማዕከል በ1 ሺህ 800 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ ባለ 10 ወለል ሕንጻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለተኝቶ ታካሚዎች አገልግሎት የሚሰጥ 320 አልጋ ያለው ሲሆን ÷ ይህም ላለፉት 91 ዓመታት የነበረውን የዘውዲቱ ሆስፒታል ታካሚ አገልግሎት በእጥፍ ያሳድጋል ነው ያሉት።
ሆስፒታሉ ለሕክምና ባለሙያው እና ለታካሚው በሚመች መልኩ የተገነባ መሆኑን ከንቲባዋ አስረድተዋል፡፡
አሁን ላይ የሕክምናው ዘርፍ በደረሰበት ዘመናዊ የሕክምና መሳሪያዎች የተደራጀና የራሱ ኦክስጂን ማምረቻ እንዳለው አመልክተዋል፡፡
ሆስፒታሉ አስተዳሩ አዲስ አበባን የሜዲካል ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ለጀመረው ሥራ ተደማሪ አቅም እንደሚፈጥርም ገልጸዋል፡፡