አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኮሪደር ልማት ሥራ የሕዝባዊ ሥፍራዎችን ደረጃ ከፍ በማድረግ ዕሳቤ በሁሉም ደረጃ በመላው ኢትዮጵያ እየተተገበረ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ ዛሬ ጠዋት በአማራ ክልላዊ መንግሥት ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር መቀመጫ በሆነችው ከሚሴ ተገኝቼ ለሕዝቡ መልዕክት አስተላልፌያለሁ ብለዋል።
በአማራ ክልል ከጎበኘኋቸው ዞኖች እስካሁን ያልጎበኘሁት ዞን በመሆኑ ጉብኝቱን የተለየ ያደርገዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ የከሚሴ የኮሪደር ልማት ሥራ በጅምር ደረጃ ያለ ቢሆንም የ1 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ እና የእግረኛ መንገድ ሥራዎች የሚመሰገኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የኮሪደር ልማት ሥራ የሕዝባዊ ሥፍራዎችን ደረጃ ከፍ በማድረግ ዕሳቤ በሁሉም ደረጃ በመላው ኢትዮጵያ እየተተገበረ መሆኑን ያሳያሉም ነው ያሉት።
በከተማዋ ለሌማት ትሩፋት ሥራችን አስተዋጽዖ እያበረከተ ያለውን የኤልፎራ አግሮ-ኢንዱስትሪ የተቀናጀ የግብርና ልማት ፋብሪካንም ጎብኝተናል ብለዋል በመልዕክታቸው።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!