አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና ኤክስቴንሽን መርሐ ግብር ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እያገዘ ነው አለ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ።
በክልሉ የከተማ ጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ንቅናቄ መድረክ “የከተማ ጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምን በማጠናከር የማሕበረሰቡን የጤና ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በአዲሱ የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ በገጠር ጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡
የተቀዛቀዘውን የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ለማነቃቃት በክልሉ ከ1 ሺህ 200 በላይ ባለሙያዎች የተሳተፉበት የገጠር ጤና ኤክስቴንሽን ንቅናቄ መካሄዱን ጠቅሰዋል።
የከተማ ጤና ኤክስቴንሽንን መደገፍና ማጠናከር በከተሞች ጤናው የበለጸገ ማሕበረሰብ ለመፍጠር አጋዥ በመሆኑ የንቅናቄ መድረኩ እንደተዘጋጀ አመላክተዋል፡፡
እንደ ሀገር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን አንስተው÷ ከልየታ ጀምሮ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ኃላፊነት ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህም መድረኩ ወባን ጨምሮ ተላላፊ የሆኑ በሽታዎች ላይ በትኩረት ለመስራት የሚያስችል እንደሆነ መናገራቸውን የቢሮው ሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ገዙ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!