አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያ ሩዋንዳን 2 ለ 0 አሸንፋለች።
በዛሬው ዕለት በተጀመረው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ከ17 ዓመት በታች የማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያን አሸናፊ ያደረጉትን ሁለት ግቦችን ዳዊት ካሳ እና ሁዘይፋ ሻፊ አስቆጥረዋል።
በተመሳሳይ ውድድር ቀን 7፡00 ላይ በተካሄደው የመክፈቻ ጨዋታ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን 2 ለ 2 በሆነ የአቻ ውጤት ተለያይተዋል።
እንዲሁም መርሐ ግብሩ ቀጥሎ ሲካሄድ ምሽት 11:00 ሰዓት ላይ ታንዛኒያ ከ ሱዳን እንዲሁም ምሽት 2:00 ቡሩንዲ ከ ዩጋንዳ ይጫወታሉ።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!