የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ለኮፕ 32 አስተናጋጅነት መመረጧ በዘርፉ ላላት ቁርጠኝነት እውቅና የሰጠ ነው – ኢጋድ

By Adimasu Aragawu

November 15, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባኤን እንድታስተናግድ መመረጧ በዘርፉ ላላት ቁርጠኝነት እውቅና የሰጠ ነው አለ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ)።

የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታዘጋጅ መመረጧን ተከትሎ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ ጉባኤውን እንድታዘጋጅ መመረጧ በአየር ንብረት እና ልማት ያላት መሪነት እያደገ መምጣቱን የሚያሳይ ነው።

የኢትዮጵያ መመረጥ ሀገሪቱ ሥነ ምህዳርን በመመለስ፣ ዘላቂ እድገት እና የማይበገር አቅም ለመገንባት እያከናወነች ለምትገኘው ጠንካራ ስራ እና ቁርጠኝነት እውቅና የሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።

ጉባኤው ለኢጋድ ቀጣና ወሳኝ መድረክ እንደሆነ በመግለጽ÷ ድርቅ፣ የአየር ንብረት ለውጥ የፈጠረው የዜጎች መፈናቀልና የውሃ እጥረትን ጨምሮ ሌሎች አንገብጋቢ አጀንዳዎች የበለጠ ትኩረት እንዲሰጣቸው ያደርጋልም ነው ያሉት።

ድርጅቱ ከኢትዮጵያ፣ ከተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ጽህፈት ቤት እና ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር ጉባኤው የአፍሪካ የቅድሚያ ትኩረቶች ማዕከል ያደረገና ለአየር ንብረት ለውጥ ዘላቂ መፍትሄ የሚገኝበት እንዲሆን በትብብር እንደሚሰራ አመላክተዋል።

ኢጋድ በጉባኤው ላይ የአየር ንብረት ፋይናንስን የሚያጠናክሩ፣ ቀጣናዊ ትብብርን የሚያሻሽሉና የአፍሪካ የአየር ንብረት ቀውስን ለመፍታት በሚደግፉ ስምምነቶች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆምም አረጋግጠዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!