አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት እንድትሆን እንደ ሀገር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው አሉ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)።
የባሕር በር ባለቤትነት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የማስጠበቅ የሕልውና ጉዳይ መሆኑንም ተናግረዋል።
አሁን በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚ የሚመጥን የወጪና ገቢ ዕቃዎችን ማስተናገድ የሚችል የባሕር በር አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በባሕር ዳር ከተማ በተካሄደ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ላይ እንደገለጹት÷ አሁን ላይ ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባውም ሆነ ወደ ውጭ የምትልከው ምርት በዓይነትም ሆነ በመጠን በእጅጉ ጨምሯል።
ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ በእጅጉ እያደገች መሆኑን ጠቁመው÷ ይህን ማስተናገድ የሚችል ብዙ ወደብ ያስፈልጋታል ብለዋል።
መንግስት ኢትዮጵያ የባሕር በር እንደሚያስፈልጋት አምኖ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን በመግለጽ÷ ይህን ጥረት ሁሉም ዜጋ ሊደግፈው ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!