ፋና ስብስብ

ፋና 80 የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ዛሬም ቀጥሎ ይካሄዳል

By sosina alemayehu

November 16, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና 80 የመጀመሪያው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር 5ኛ ሳምንት ውድድር በዛሬው ዕለት ቀጥሎ ይካሄዳል።

የፋና 80 ምዕራፍ 1፣ 2 እና 3 ውድድሮች አሸናፊ ቡድኖች በመጀመሪያው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ብርቱ ፉክክር እያደረጉ ይገኛሉ።

እናት የባህል ቡድን፣ አራት ነጥብ ዘመናዊ የዳንስ ቡድን፣ ነገስታት ዘመናዊ የዳንስ ቡድን፣ አንድ ኢትዮጵያ የባህል ቡድን፣ ጊዮን ዘመናዊ የዳንስ ቡድን እና ኢትዮጵያን የባህል ቡድን ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ።

በዚህም ዛሬ ቀን 9:00 ላይ የምድብ 1 ስድስት ቡድኖች የ5ኛ ሳምንት ውድድር በፋና ቴሌቪዥን እና በፋና+ ይተላለፋል፤ አብረውን ይሁኑ።