ቢዝነስ

ለከተሞች አገልግሎት አሰጣጥ መዘመን እገዛ የሚያደርገው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት

By Abiy Getahun

November 16, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ (ዶ/ር) መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለከተሞች አገልግሎት አሰጣጥ መዘመን ትልቅ እገዛ ያደርጋል አሉ።

በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ 10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ‘የከተሞች ዕድገት ለኢትዮጵያ ልህቀት’ በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል።

በፎረሙ ሁለተኛ ቀን ውሎ ‘የኢትዮጵያ የፐብሊክ ሰርቪስ ሪፎርም እና መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት’ በሚል በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ መኩሪያ ሀይሌ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የመንግሥት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም የተነደፈው ለሁሉም ሴክተር ነው።

ፊፎርሙ ዘመን ተሻጋሪ ተቋማት መገንባትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ እሳቤው የሰራተኛውን የአቅም ክፍተቶችን በመለየት የማብቃት ስራ መሆኑን አንስተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጭነት የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የዓለምን ምርጥ ተሞክሮዎች በመውሰድ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ መተግበሩን ጠቁመዋል።

ዓላማውም በከተሞች አገልግሎትን በአንድ ቦታ መስጠት እና የተገልጋዩን እርካታ ማረጋገጥ መሆኑን ተናግረዋል።

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለከተሞች አገልግሎት አሰጣጥ መዘመን ትልቅ እገዛ ያደርጋል ብለዋል።

ስርዓቱ ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑን ገልጸው፤ የመሶብ ዋና ማዕከል ግንባታ በዚህ ዓመት ይጀምራል ነው ያሉት።

የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የበለጸገች ሀገር የመገንባት ጥረቶች አካል መሆኑን በመግለጽ፤ ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶችን ቅድሚያ ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!