አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ከተሞች አረንጓዴ እና ለኑሮ ምቹ እንዲሆኑ በሚከናወኑ ስራዎች በከፍተኛ መነቃቃት ላይ ይገኛሉ አሉ።
‘የከተሞች ዕድገት ለኢትዮጵያ ልህቀት’ በሚል መሪ ሀሳብ በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘውን 10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ሁለተኛ ቀን ውሎ አስመልክቶ ሚኒስትሯ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም፤ ፎረሙ ከተሞች በከፍተኛ ማንሰራራት ላይ በሚገኙበት ወቅት መከበሩ የተለየ ያደርገዋል ብለዋል።
ከተሞችን አረንጓዴ እና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ መንግስት በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን አንስተው፤ ይህም በከተሞች ከፍተኛ መነቃቃት አምጥቷል ነው ያሉት።
በፎረሙ 143 ከተሞች መገኘታቸውን እና ሰባት ሺህ ኤግዚቢሽን አቅራቢዎች መታደማቸውን ገልጸው፤ የዘርፉን ተወዳዳሪነት የሚጨምሩ እና ተግዳሮቶችን የሚያቃልሉ የፓናል ውይይቶች እየተደረጉ ነው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም የድህነት ማሳያ የነበሩ ከተሞች በመንግሥት በተሰጠው ልዩ ትኩረት የብልጽግና ማሳያ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ በከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት የተከናወነው የኮሪደር ልማት ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶችን ማስገኘቱንም ጠቁመዋል።
አሁን ላይ የኮሪደር ልማት ስራ በ73 ከተሞች መስፋፋቱን ገልጸው፤ ይህም መንግሥት ለዜጎች የምትመች ሀገር ለመገንባት እየሄደበት ያለውን ርቀት የሚያሳይ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የኮሪደር ልማት ኢንዱስትሪዎች እንዲነቃቁ፣ አዳዲስ የስራ ዕድል ለመፍጠር ያስቻለ እንዲሁም የስራ ባህልን በጉልህ የቀየረ መሆኑን አመላክተዋል።
ይህም የከተሞች እንቅስቃሴን እና ገቢ በማሳደግ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲዘምን አድርጓል ብለዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!