የሀገር ውስጥ ዜና

ፎረሙ ከተሞች የቴክኖሎጂ መፍለቂያ መሆናቸው በተግባር የታየበት ነው – ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ

By Adimasu Aragawu

November 17, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 10ኛው የከተሞች ፎረም ዐውደ ርዕይ በመደመር መንግሥት ከተሞች የቴክኖሎጂ እውቀት መፍለቂያ መሆናቸው በተግባር የታየበት ነው አሉ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ።

10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም “የከተሞች ዕድገት ለኢትዮጵያ ልህቀት” በሚል መሪ ሐሳብ በአፋር ክልል ሰመራ ሎጊያ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ሚኒስትሯ ፎረሙን አስመልክቶ የተዘጋጀውን ዐውደ ርዕይ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በዚህም በዐውደ ርዕዩ በከተሞች ያለውን ከፍተኛ መነቃቃት በተጨባጭ ማየት መቻላቸውን ገልጸው÷ የዜጎች የስራ ባህል እየተቀየረ መምጣቱ በጉልህ የታየበት መሆኑን ጠቁመዋል።

መንግሥት ለከተሞች የሰጠው ትኩረት በተጨባጭ ውጤት እየተረጋገጠ መምጣቱን የተናገሩት ሚኒስትሯ÷ ከተሞች ባላቸው አቅም እና ጸጋ እየለሙ መሆናቸውን አንስተዋል።

ዐውደ ርዕዩ የከተሞች የእርስ በእርስ ግንኙነት እንዲጠናከርና ምርጥ ተሞክሮዎችን እንዲለዋወጡ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን እንዲሁም የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶቻቸውን ያሳዩበት እንደሆነ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!