የሀገር ውስጥ ዜና

የኮሪደር ልማት ቅርሶችን ጠብቆ ማቆየት አስችሏል – አቶ ኦርዲን በድሪ

By Yonas Getnet

November 17, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በክልሉ የተከናወነው የኮሪደር ልማት ቅርሶችን ጠብቆ ማቆየት አስችሏል አሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች በተመዘገበው ውጤት አሻራቸውን ላኖሩ ተቋማት እና ማህበራት የእውቅና ሽልማት አበርክተዋል።

ዓለም አቀፉ የጁገል ቅርስ ተንከባካቢ በማጣት በዩኔስኮ የተሰጠውን እውቅና የመነጠቅ አደጋ ውስጥ ገብቶ እንደነበር አቶ ኦርዲን በዚህ ወቅት አስታውሰዋል።

በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመነጪነት የተመጀረው የኮሪደር ልማት በቅርሱ ላይ የተጋረጠውን አደጋ መቀልበስ ብቻ ሳይሆን ክልሉን በሀገር አቀፍ ደረጃ ተምሳሌት ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

የኮሪደር ልማት ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር ዓለም አቀፉን የጁገል ቅርስ የመላው ኢትዮጵያና የዓለም ሀብት መሆኑን ግንዛቤ ማስረፅ መቻሉን ጠቅሰዋል።

በክልሉ በኮሪደር ልማት የተገኘው ውጤት ለቀጣይ ስራ የሚያነሳሳ መሆኑንና የተጀመሩትን የልማት ስራዎችን ፍጥነት በመጨመር በማጠናቀቅ በቀጣይ ጅምር ስኬቶችን ለማስፋት ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!