አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ አቀረቡ።
አምባሳደሩ በዚህ ወቅት÷ በሚኖራቸው የሥራ ጊዜ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ቀጣናዊ የትስስር ጉዳዮች ላይ የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ ሰላም እና መረጋጋት እንዲስፋፋ ለማገዝ በትኩረት እንደሚሰሩ ነው ያስገነዘቡት፡፡
የሁለቱን ሀገራት ትብብር ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ እንዲሁም የጋራ ዕሴቶችን ለማስጠበቅ ቁርጠኛ እንደሆኑ መግለጻቸውንም ኤምባሲው ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!