ቴክ

ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልገው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሐሰተኛ መረጃ …

By abel neway

November 18, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዲጂታል ዓለም ግዙፍ ከሚባሉት ኩባንያዎች መካከል ቀዳሚ የሆነው ጉግል ኩባንያ ኃላፊ ሱንዳር ፒቻይ ለአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ከፍተኛ መጠን ያለው መዋዕለ ንዋይ እየፈሰሰ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል።

ቴክኖሎጂው ይዞት የሚመጣው ዕድል ላቅ ያለ ቢሆንም አብሮት የሚመጣውን ስጋት በመገንዘብ ተገቢው ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የትኛውም ድርጅት ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሐሰተኛ መረጃ ስጋት ሊድን አይችልም በማለት ጠቅሰው፤ በዚህ ረገድ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ኃላፊው ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በሁኑ ሰዓት ለአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚፈሰውን መዋለ ንዋይ የሚመጥን ጥንቃቄ ይፈልጋል ብለዋል።

የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዕድል ብቻ ሳይሆን ስጋቱም ከግንዛቤ መግባት እንዳለበት ተናግረዋል።

ሱንዳር ፒቻይ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትሉም አስገንዝበዋል።

ጉግል ኩባንያ ጉዳዩ ያሰጋው እንደሆነ የተጠየቁት ሃላፊው ጉዳዩ ለጎግል ኩባናያም ጭምር እንቅልፍ የሚነሳ ጉዳይ መሆኑን በመጠቆም ከጉዳቱ ሊያመልጥ እንደማይችል ተናግረዋል፡፡