አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ብልሹ አሰራርን ለመቅረፍ ያስችላል አሉ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሱልጣን አብዱሰላም።
አፈ ጉባኤው ከቀናት በፊት ተመርቆ ሥራ የጀመረው የሀረሪ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የጎበኙ ሲሆን÷ በህዝብ ሲነሱ ለቆዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል።
በማዕከሉ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከወረቀት ንክኪ ነጻ የሆኑና ሙሉ ለሙሉ በቴክኖሎጂ የታገዙ መሆናቸው ብልሹ አሰራርን ለመቅረፍ እንደሚያግዝም አመላክተዋል፡፡
በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለውጥ ለማምጣት በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው÷ ማዕከሉ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ነው ብለዋል።
በማዕከሉ የሚሰጡ አገልግሎቶች ጊዜ ቆጣቢና የዜጎችን እንግልት የሚቀርፉ መሆናቸውን አንስተው÷ መንግሥት ለዜጎች ጥያቄ ፈጣን ምላሽ እየሰጠ መሆኑን በተግባር እያሳየ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በማዕከሉ የሚሰጡ አገልግሎቶች ዜጎችን ከተጨማሪ ወጪና እንግልት የሚታደጉ ናቸው ማለታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሔኖክ ሙሉነህ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!