ስፓርት

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ልማት በቅርቡ ብርቱ ተፎካካሪ ለመሆን ያስችላል – ቤንጃሚን ዚመር

By Yonas Getnet

November 19, 2025

‎አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የጀመረችው የእግር ኳስ ልማት በቅርቡ በታላላቅ መድረኮች ተፎካካሪ የሚያደርጋት ነው አሉ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር ፡፡

‎የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ2ኛው የምድብ ጨዋታ ደቡብ ሱዳንን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወቃል፡፡

ይህን ተከትሎ ከፋና+ ጋር ቆይታ ያደረጉት አሠልጣኝ ቤንጃሚን ÷ ጨዋታውን ባቀድነው ልክ ተቆጣጥረን ተጫውተናል ብለዋል፡፡

ይህም ተጋጣሚያችን ደቡብ ሱዳን ላይ ብልጫ ወስደን እንድናሸንፍ ረድቶናል ነው ያሉት፡፡ ‎ ‎በኢትዮጵያ ትልቅ የእግር ኳስ አቅም እንዳለ ተመልክቻለሁ ያሉት አሠልጣኙ ÷ መንግስት እንዲሁም የሀገሪቱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ለስፖርቱ ልማት የሰጡት ትኩረት አበረታች መሆኑን ጠቅሰዋል። ‎ ‎በአሁን ሰዓት አዳጊዎች ላይ እየተሠራ ያለው ሥራ ኢትዮጵያን በቅርቡ በአህጉር ከፍ ሲልም በዓለም አቀፍ መድረኮች ተፎካካሪ ሊያደርጋት እንደሚችል አመልክተዋል፡፡ ‎ ‎የኢትዮጵያን ባለተሰጥኦ አዳጊዎች አቅም በአግባቡ ለመጠቀም በፕሮጀክት ታቅፈው ተገቢ ስልጠና መስጠት እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡ ‎ ‎የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከምድቡ ያደረጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች በማሸነፍ በ6 ነጥብ ምድቡን እየመራ ይገኛል፡፡ ‎ ‎ በሙባረክ ፋንታው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!