የሀገር ውስጥ ዜና

የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

By sosina alemayehu

November 19, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማሌዥያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም የዓድዋ ድል መታሰቢያ እና አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎብኝተዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ እና አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ የሚያደርጉት ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡