አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በተያዘው በጀት ዓመቱ 250 ሚሊየን ቶን መኖ ለማምረት እየተሰራ ነው አለ የግብርና ሚኒስቴር።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 91 ሚሊየን ቶን መኖ ማምረት ተችሏል።
ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ፣ ቢሾፍቱ፣ አዳማ እና ባሕር ዳር ብቻ የነበሩት የመኖ ማቀነባበሪያዎች አሁን ላይ በሁሉም ክልል የዞን ከተሞች እንዲስፋፉ ተደርጓል ብለዋል።
በቅርቡም 15 የመኖ ማቀነባበሪያ ማሽነሪዎች ለክልሎች መሰራጨታቸውን ተናግረዋል።
መኖ በየቦታው እንዲመረት እና ማቀነባበሪያዎችም እንዲስፋፉ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው÷ በየጊዜው የመኖ ዋጋ ላይ ሲነሳ የነበረውን 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ ለማስነሳት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ አንስተዋል።
በዙፋን ካሳሁን
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!