አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የማሌዢያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽንን ጎብኝተዋል።
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባበል ያደረጉት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ፤ ጉብኝቱ የማሌዢያ እና የአፍሪካን ግንኙነት የሚያጠናክር ታሪካዊ ጉብኝት መሆኑን ተናግረዋል።
የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር የአፍሪካ ህብረትን ሲጎበኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የአፍሪካ ማሌዢያን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ጉብኝቱ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑን አመልክተዋል።
በፈረንጆቹ 2024 የአፍሪካ ማሌዢያ የንግድ ትስስር 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላርን መሻገሩን ጠቅሰው፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት የንግድ ትስስሩ የ20 በመቶ ዕድገት ማሳየቱንም አንስተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!