አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ኢብራሂም በኢትዮጵያ ያደረጉትን የሦስት ቀናት የስራ ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አሸናኘት አድርገውላቸዋል።
በኢትዮጵያ ቆይታቸው በብሔራዊ ቤተመንግሥት ይፋዊ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት የተደረገላቸው የማሌዢያው ጠቅላይ ሚኒስትር÷ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ውይይት አድርገዋል።
መርሐ ግብሩ የወዳጅነት ዛፍ የመትከል ሥነ ሥርዓት፣ የብሔራዊ ቤተመንግሥት ጉብኝት፣ የሁለትዮሽ ውይይት፣ የሰነዶች ልውውጥ ብሎም በቱሪዝም፣ ጤና፣ አየር ትራንስፖርት አገልግሎት፣ በኳላ ላምፑር ከተማ ምክር ቤት እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትብብር ስምምነቶችን ያካተተ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባለፈው ዓመት በማሌዥያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
በለይኩን ዓለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!