የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ማሌዢያ ለአፍሪካና እስያ ድልድይ ናቸው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

By Abiy Getahun

November 20, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ እና ማሌዢያ ለአፍሪካና ለእስያ ሀገራት ድልድይ ናቸው አሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ኢብራሂም በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስርት ዐቢይ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ሁለቱ ሀገራት ለአፍሪካና ለእስያ ሀገራት ድልድይ ናቸው፡፡

ሀገራቱን በሚጠቅሙ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸው፤ ይህ የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጉብኝት ሌላ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ማሌዢያ ለጋራ ራዕይ ወዳጅነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ዓለምን የመሳብ ትልቅ አቅም አላት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዚህም የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ጉባኤን (ኮፕ32) እንድታስተናግድ መመረጧን አውስተዋል፡፡

በተጨማሪም በኢንዱስትሪ፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በቱሪዝም እና ሌሎች መስኮች በጋራ ለመስራት ሰፊ ውይይት መደረጉን አብራርተዋል።

የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት የቆየ መሆኑን የገለጹት የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ኢብራሂም በበኩላቸው፤ በቀጣይ ግንኙነቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ በርካታ ባህል እና የተለያየ እምነት ያላቸው ዜጎች የሚኖሩባት ሀገር መሆኗን ጠቅሰው፤ ሁሉም ተከባብሮ እንደሚኖርባት ገልጸዋል፡፡

ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ያደረጉት ጉብኝት ፍሬያማ እንደነበር ገልጸው ወዳጅነታቸውን ይበልጥ ያጠናከረ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!