የሀገር ውስጥ ዜና

ወይዘሮ አዳነች አቤቤና ኢንጂነር ታከለ ኡማ አዲስ በተሾሙበት የስራ ቦታ ዛሬ በመገኘት የስራ ርክክብ አደረጉ

By Tibebu Kebede

August 19, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የመዲናዋ ምክትል ከንቲባ በመሆን የተሾሙት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ላለፉት ሁለት ዓመታት በምክትል ከንቲባነት ካገለገሉት ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሀላፊነቱን ተረክበዋል።

በከንቲባ ፅህፈት ቤት በተካሄደ የስራ ርክክብ ስነ ስርዓት ላይም የስራ ኃላፊዎቹ በአዲስ አበባ አጠቃላይ የሥራ ሂደት ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።