አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የባሕር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት የጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሐኪም በነበሩት ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ላይ የግድያ ወንጀል በፈፀመው ተከሳሽ ላይ የ25 ዓመት ጽኑ እስራት ወስኗል።
ፍ/ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት በዶክተር አንዷለም ዳኘ የግድያ ጉዳይ ላይ የቀረበውን መረጃ እና ማስረጃ መሰረት አድርጎ ውሳኔ አሳልፏል።
በዶክተሩ ላይ ግድያው የተፈፀመው ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት ላይ ባሕር ዳር ከተማ የግል መኪናቸውን በሚያሽከረክሩበት ወቅት ጠብቆና ተዘጋጅቶ በጥይት ተኩሶ መግደሉን ፍርድ ቤቱ በቀረበ ማስረጃ አረጋግጧል።
በዚሁ ዕለት ምሽት ላይ በተመሳሳይ በሌላ የሕክምና ዶክተር ላይ ጥይት በመተኮስ የመኪናውን አካል በመምታት የግድያ ወንጀል ሙከራ ስለመደረጉም ፍርድ ቤቱ አመልክቷል።
የግድያ ወንጀሉ ከተፈጸመ ጊዜ ጀምሮ መረጃና ማስረጃዎችን በማሰባሰብ የተጠናከረ የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ ሥራው ተጠናቅቆ ለፍርድ ቤቱ ቀርቧል።
በዚህ የምርመራ ሒደት ከክልሉ ፖሊስ ዋና መምሪያ እና ከከተማ አስተዳደሩ የምርመራ ቡድን ተዋቅሮ መረጃና ማስረጃዎችን በማሰባሰብ የወንጀሉን አፈፃፀምና ፈጻሚውን ማወቅ እንደተቻለ መጠቀሱን ኢዜአ ነው የዘገበው፡፡
ፍርድ ቤቱም የቀረቡለትን የምርመራ ውጤቶች መሰረት በማድረግ በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት ወንጀሉን በፈጸመው ግለሰብ እሱባለው ነበረ ላይ የ25 ዓመት ጽኑ እስራት ወስኖበታል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!