የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ፖሊስ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን እጩ መኮንኖች አስመረቀ

By Adimasu Aragawu

November 22, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ፖሊስ ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በራስ አቅም ያሰለጠናቸውን እጩ መኮንኖች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት÷ በስልጠና ያገኛችሁትን ተጨማሪ አቅም ከማሕበረሰቡ፣ ከሌሎች የፀጥታ ተቋማትና የሙያ ባልደረቦቻችሁ ጋር በመቀናጀት የከተማችንን ሰላምና ፀጥታ የምታፀኑበት እንደሚሆን እምነት አለኝ ብለዋል።

ተመራቂ መኮንኖች ወደ ሥራ ሲሰማሩ ሙያቸውን በታማኝነት፣ በቅንነት፣ ለእውነት በመወገንና በአርቆ አሳቢነት በመመራት ሐቀኛ የሕዝብ አገልጋይነትን በብቃት እንዲወጡ አስገንዝበዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ኮሌጁ በምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ ለመሆን ለሰነቀው ራዕይ እንደ ሁልጊዜውም ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Facebook https://web.facebook.com/fanasport Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!