አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጆሃንስበርግ እየተካሄደ በሚገኘው የቡድን 20 የመሪዎች ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው።
የቡድን 20 አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
ጉባዔው “አጋርነት፣ እኩልነት እና ዘላቂነት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በጉባዔው መክፈቻ ላይ የወቅቱ የቡድን 20 አባል ሀገራት ሊቀ መንበር እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ስሪል ራማፎሳ እና የአባል ሀገራት መሪዎችም ተገኝተዋል።