የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ጋር ተወያዩ

By abel neway

November 22, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢኮኖሚ፣ በባሕል ወዳጅነት ግንኙነት፣ በዘላቂ ልማት እና የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን በሚያካትቱ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ምክክር አድርገዋል፡፡

ውይይቱ በጆሃንስበርግ እየተካሄደ ከሚገኘው የቡድን 20 የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን ነው የተከናወነው፡፡