የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከፊንላንድ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By abel neway

November 22, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፊንላንድ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በቀጣናዊ፣ ባለብዙ ወገን ትብብር እና በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

እንዲሁም በአየር ንብረት ጥበቃ ሥራ እና በኢትዮጵያ በተከፈተው የኢኮኖሚ ምኅዳር ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ውይይቱ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ትስስር እና የጋራ ጥቅም ትብብር በማጠናከር ላይ ያለውን አቋም ያጠናከረ እንደነበር አመልክተዋል፡፡