የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር ተወያዩ

By abel neway

November 22, 2025

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በአየር ንብረት ጥበቃ ሥራ ትብብር እና የጋራ ትኩረት በሚሹ የባለብዙወገን ጉዳዮች ላይ መክረናል ብለዋል፡፡

እንዲሁም የሀገራቱን ትብብር በሚያጠናክሩ እና ዘላቂ እድገትን በሚያሳድጉ የኢንቨስትመንት እድሎች ላይ መወያየታቸውን አመልክተዋል።

ውይይቱ በጆሃንስበርግ እየተካሄደ ከሚገኘው የቡድን 20 የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን ነው የተደረገው፡፡