አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል የከተማ ተቀናቃኙን ቶተንሃምን በሜዳው ኤምሬትስ ይገጥማል፡፡
የሊጉ መሪ አርሰናል ዛሬ ምሽት 1፡30 ላይ በሚደረገው የለንደን ደርቢ ጨዋታ መሪነቱን ለማጠናከር ሲገባ ከከተማ ባላንጣው ቶተንሃም ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል።
አርሰናል ጨዋታውን ካሸነፈ ነጥቡን 29 በማድረስ ከተከታዩ ቼልሲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት ከፍ ያደርጋል።
ቶተንሃም ነጥቡን 21 በማድረስ ወደ አራተኛ ደረጃ ከፍ ለማለት ከባድ ትንቅንቅ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎ 11:00 ላይ በሚደረግ የሊጉ ጨዋታ ሊድስ ዩናይትድ አስቶን ቪላን ያስተናግዳል።
ትናንት በተደረጉ የሊጉ 12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታዎች ኒውካስል ዩናይትድ ማንቼስተር ሲቲን 2 ለ 1 ሲያሸንፍ፤ ሊቨርፑል በሜዳው በኖቲንግሃም ፎረስት የ3 ለ 0 ሽንፈት ደርሶበታል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!