አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ)የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በቡድን 20 ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ በትብብር የምትሰራ፣ ሀሳብ የምታመነጭ እና መፍትሔ የምታቀርብ ሀገር እንደሆነች ማሳየት ተችሏል አሉ።
ሚኒስትሩ በቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያን ተሳትፎ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በስብሰባው መሳተፏ ለሀገር ትልቅ ፋይዳ አለው።
ስብሰባው ላይ የሀገራችንን አቋም፣ ፍላጎት እንዲሁም አጠቃላይ እንደ አፍሪካ መነሳት ያለባቸውን አጀንዳዎች አንስተናል ብለዋል።
ከቡድን 20 ስብሰባ ጎን ለጎን በሁለትዮሽ መድረኮች የበርካታ ሀገራትን መሪዎች እና የዓለም ዓቀፍ ተቋማትን ሃላፊዎችን በማግኘት የሀሳብ ልውውጥ መደረጉን ገልጸው፤ ይህም ትብብርን እና ግንኙነትን ለማጠናከር ጥሩ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል።
በስብሰባው ኢኮኖሚያዊ ስርዓቱ ፍትሃዊ እና የሁሉንም ዕድገት የሚያሳልጥ እንዲሆን፣ በአፍሪካ ትልቅ አቅም እንዳለ እና በኢትዮጵያ የተገኙ ውጤቶችን ማሳየት መቻሉን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ለጋራ ተጠቃሚነት የፋይናንስ ስርዓቱን፣ የአፍሪካ ሀገራትን ሚና እንዴት ማጉላት እንደሚያስፈልግ አቋሟን ማንጸባረቋን ገልጸዋል።
በአካባቢ ጥበቃ እና አየር ንብረት ላይ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ሀገሮች በትብብር መስራት የሚችሉበትን መንገድ ማመላከት እንደተቻለም ጠቁመዋል።
በዚህ መልኩ ኢትዮጵያ ድጋፍ የምትጠይቅ ሳትሆነ የመፍትሔ አካል የሆነች፣ በትብብርና በአጋርነት የምትሰራ፣ ሀሳብ የምታመነጭ እና መፍትሔ የምታቀርብ ሀገር እንደሆነች ለማሳየት ተችሏል ነው ያሉት።
የአፍሪካ ሀገራት ዕዳ ለመክፈል የሚያወጡት ወጪ የልማት እንቅስቃሴያቸውን ያገደ እንደሆነ እና ኢትዮጵያ የንግድ ብድርን በማቆም በውስጥ አቅም አጠቃላይ የኢኮኖሚ አቋሟን የተሻለ ለማድረግ የሄደችበትን ርቀት በማሳየት ይህ እንቅስቃሴ በሁሉም ሊደገፍ እንደሚገባ ማስረዳት መቻሉን አንስተዋል።
ዕዳን በመክፈል ፋንታ በልማት የሚወጣ ወጪ ዞሮ ዞሮ ሁሉንም ተጠቃሚ እንደሚያደርግ እንዲሁም የዕዳው ጉዳይ ከአየር ንብረት ለውጥ ተግባሮች ጋር ተያይዘው መታየት እንዳለበትም ማስረዳት ተችሏል ብለዋል።
አፍሪካ ለዓለም ሙቀት መጨመር አሉታዊ አስተዋጽዖ ያበረከተች እንዳልሆነችና አሁን ደግሞ ልማታችንን የሚያግዝ አረንጓዴ የሆነ እና ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ማድረግ እንደሚገባ በመግለጽ ኢትዮጵያ አቋሟን ማንጸባረቋን አብራርተዋል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!