አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኮፕ32ን በኢትዮጵያ ስናዘጋጅ ከብራዚል የምንወስደው ብዙ ጠቃሚ ልምዶች አሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቡድን 20 አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን ከብራዚሉ ፕሬዚዳንት ሉዊዝ ኢናችዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር ጥሩ ውይይት ማካሄዳቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።
ውይይቱ በኢኮኖሚ እና ዘላቂ የመሠረተ ልማት ጉዳዮች ላይ አተኩረን የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን የምናጠናክርባቸውን እድሎች አስመልክቶ የተካሄደ ነበር ብለዋል።
ብራዚል በቅርቡ የተካሄደው የኮፕ30 አስተናጋጅ ሀገር እንደመሆኗ ኮፕ32ን በኢትዮጵያ ስናዘጋጅ ከብራዚል የምንወስደው ብዙ ጠቃሚ ልምዶች አሉ ብለዋል።
የዓለም የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራን የሚያራምድ በሚገባ የተሰናዳ መስተንግዶ እንዲኖረን ከልምዶች የተገኙ ሃሳቦችን መለዋወጡን አጠናክረን ለመቀጠል አቅደናል ሲሉ አስረድተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!