አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተገልጋዮችን እንግልት በማስቀረት በክልሉ የአገልግሎት አሰጣጥን አቀላጥፏል አሉ፡፡
ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ የጅማ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የጎበኙ ሲሆን፥ ማዕከሉ የተደራጀባቸው ቴክኖሎጂዎችና አግልግሎት አሰጣጡ ለሌሎች ከተሞችም ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል።
ጅማ ከተማን ጨምሮ በክልሉ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአምስት ከተሞች ተግባራዊ መደረጉን ገልጸው፥ በቀጣይም በክልሉ 28 ከተሞች አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በምቹ የስራ ከባቢ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ማህበረሰቡ በአንድ ማዕከል ቀልጣፋና ከሙስና የጸዳ አግልግሎት እንዲያገኝ በማስቻል ረገድ ማዕከሉ የላቀ ሚና እየተወጣ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ከመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ባሻገር በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ወደ ቀበሌ በመውረድ ተግባራዊ የተደረገው መዋቅር ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል ነው ያሉት፡፡
25 አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ያቀፈ የጅማ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል ከብልሹ አሰራር የጸዳ ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የከተማ ከንቲባ አቶ ጣሃ ቀመር ተናግረዋል።
በወርቅአፈራው ያለው